አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በኢትዮጵያ የስፔን አምባሳደር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በኢትዮጵያ የስፔን አምባሳደር ጉሌርሞ አንቶኒዮ ሎፔዝ ማክ-ሌላን ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸውም፤ በኢትዮጵያና ስፔን መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
በዚህም በተለያዩ መስኮች በትብብር መስራት ስለሚቻልበትና የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።