ሰሜን ኮሪያ ስምምነቶችን እንድታከብር ደቡብ ኮሪያ ጠየቀች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ኮሪያ የአንድነት ሚኒስቴር ሰሜን ከኮሪያ ከዚህ ደቀም በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈረሙ ስምምነቶችን አክብራ እንድትንቀሳቀስ ጠየቀ።
ሚኒስቴሩ መግለጫውን ያወጣው ሰሜን ኮሪያ በደቡብ ኮሪያ ላይ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ማስጠንቀቂያ ማስተላለፏን ተከትሎ መሆኑም ታውቋል።
ደቡብ ኮሪያ እና ሰሜን ኮሪያ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሱ ስምምነቶችንን ማክበር ይገባልም ብሏል ሚኒስቴሩ በመግለጫው።
የሀገሪቱ መንግስት በአሁኑ ሰዓት እየተካሄዱ ያሉ ሁነቶችን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየተመለከተው እንደሚገኝም አመላክቷል።
ደቡብ ኮሪያ እና ሰሜን ኮሪያ ከዚህ ቀደምም በሁለቱ ሀገራት ድንበር መካከል በሚገኘው ከጦር መሳሪያ ነፃ በሆነው ቀጠና ላይ የጦር መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በመቀጠልም ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ በደቡብ ኮሪያ ያሉ የከዱኝ ዜጎች ጠብ አጫሪ መልእክቶችን የያዙ በራሪ ወረቀቶችን በፊኛ በማድረግ ወደ እኔ እየላኩ ነው በማለት ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያላትን ሁሉንም ግንኙነቶቿን ማቋረጧም አይዘነጋም።
ምንጭ፦ reuters.com