ፀጋዎችን በአግባቡ ለመጠቀም ጠንካራ የስራ ባህል ማዳበር እንደሚገባ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጸጋዎቻችንን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችል ጠንካራ የስራ ባህል ማዳበር ይገባል ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ፡፡
”ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፣ ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር” በሚል መሪ ሐሳብ የምክክር መድረክ በአሶሳ መካሄዱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያን ክብር ለማስጠበቅ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እና የተረጅነት አስተሳሰብን መቅረፍ እደሚገባ አቶ አሻድሊ በመድረኩ ላይ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
ፀጋዎቻችንን ከመረዳት ባለፈ በአግባቡ ለመጠቀም ጠንካራ የስራ ባህል ማዳበር አለብን ያሉት ርዕሰ መሥተዳድሩ÷ በቀጣይ በክልሉ ያለውን የተፈጥሮ ፀጋ በመጠቀም ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡