በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የልማት ስራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት እና ተወካዮች በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎበኙ።
የአመራር አባላቱና ተወካዮቹ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ግንባታን ተመልክተዋል።
በተጨማሪም ግንባታው እየተጠናቀቀ የሚገኘውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ግንባታንም መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎቹ አመራር አባላት ሰሞኑን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የልማት ስራዎች ሲጎበኙ መቆየታቸውም ታውቋል።
ከጉብኝቱ በኋላ ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል።