Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የኮርያ ጦርነት ዘማቾች መታሰቢያ ማዕከልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኮሪያ ጦርነት መታሰቢያ ሃውልት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠው የኢትዮጵያ የኮርያ ጦርነት ዘማቾች መታሰቢያ ማዕከልን ጎብኝተዋል።

በደቡብ ኮርያ ቹንቺዮን ከተማ ሲደርሱም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ይህ መታሰቢያ ከደቡብ ኮሪያ እና የተባበሩት መንግሥታት ኃይሎች ጋር መስዋዕትነት የከፈለው እና አስተዋፅዖ ያበረከተው የኢትዮጵያ ቃኘው ሻለቃ በክብር የሚታወስበት ሲሆን የኢትዮጵያን እና የደቡብ ኮሪያ ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር የተሰራ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.