Fana: At a Speed of Life!

ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ በልማት ሥራ ምክንያት በከፊል ዝግ እንደሚሆን ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ በልማት ሥራ ምክንያት በከፊል ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በመንገድ ኮሪደር ልማት እና የአስፓልት ንጣፍ ስራ ምክንያት ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስደው ዋናው መንገድ በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረትም፡-

– ከለገሐር በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ

– ከእስጢፋኖስ በቀጥታ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ

-ከኡራኤል በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ

እንዲሁም በውስጥ ለውስጥ ወደ ዋናው ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ
የሚወስዱ መንገዶች ከግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በየዕለቱ የልማት ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:30 ሰዓት ለተሽከርካሪ በከፊል ዝግ ይሆናሉ፡፡

ስለሆነም አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥማቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ አዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.