Fana: At a Speed of Life!

አብርሃም በላይ(ዶ/ር) ከፋኦ የስራ ሃላፊዎች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)ከተባበሩት መንግስታት የምግብና ግብርና ድርጅት (ፋኦ) ልኡካን ጋር በቀጣይ የትብብር መስኮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የምግብና ግብርና ድርጅት (ፋኦ) የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሰርቪስ ሃላፊ ጂዮቫኒ ሙኖዝ፣ በኢትዮጵያ የፋኦ ተወካይ ፋራይ ዚሙድዚ እና ልዑካን ጋር በተደረገው በዚህ ውይይት የመስኖ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ብርሃኑ ሌንጂሶ(ዶ/ር)ም ተገኝተዋል፡፡

ውይይቱ በዋናነት በመጪ ፍላግሺፕ ፕሮጀክች ላይ የቴክኒክ ድጋፍ ማቅረብ፣ የመስኖ ኮዶችን፣ መመሪያዎችን እና የሕግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት ላይ ያተኮረ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

ፋኦ በጂ.አይ.ኤስ ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረቱ የአስተዳደር መረጃ ስርዓትን ከፕሮጀክቶቹ ጋር በማዋሃድ የመረጃ አያያዝ አቅምን ማጎልበት ላይ አብሮ ለመስራት መስማማቱም ተሰምቷል፡፡

በተጨማሪም ቡድኑ ለመስኖ ዲዛይን፣ ለግንባታ፣ ለአሰራር እና ለጥገና እንዲሁም የመስኖ ኢንቨስትመንት ትንተና እና የታሪፍ መቼቶች ላይ ያተኮረ ድጋፍ በሚመለከት መወያየታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሚኒስቴሩ ከፋኦ ጋር ያለው ትብብር የግብርና መሠረተ ልማትንና ዘላቂነትን ለማጎልበት በሚደረገው ጥረት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.