Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች ከ ሲ 40 ከተሞች ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሲ 40 ከተሞች ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ከሆኑት ማርክ ዋትስ ጋር ተወይተዋል፡፡

በሲንጋፖር የዓለም የከተሞች ፎረም እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፥ ከፎረሙ ጎን ለጎን የሲ 40 ከተሞች ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ማርክ ዋትስ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም “በከተማችን እና በሲ40 መካከል ያለውን ትብብር ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ተወያይተናል” ብለዋል።

በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም፣ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በማስፋፋት እንዲሁም የህዝብ የጋራ መጠቀሚያ ስፍራዎችን በመገንባት ላይ የተጀመረውን ትብብር ማሳደግን ጨምሮ በሌሎች ተዛማች አጀንዳዎች ላይ በቀጣይ አብሮ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መምከራቸውን ጠቅሰዋል።

አክለውም ከፈረንጆቹ 2007 ጀምሮ አዲስ አበባ አባል የሆነችበት የሲ 40 ከተሞች ድርጅት ባለፉት ጊዜያት የተለያዩ የፋይናንስ፣ የቴክኒካልና የአቅም ግንባታ ድጋፎችን ለመዲናዋ ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.