Fana: At a Speed of Life!

አብረሃም በላይ (ዶ/ር) ሠራዊታችን ሀገርን ከብተና ለመታደግ በሚዋደቅበት ወቅት ፈተና ሳይበግራቸው አገልግለዋል – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አብረሃም በላይ (ዶ/ር) መከላከያ ሚኒስትር በነበሩበት ጊዜ ሠራዊታችን ሀገርን ከብተና ለመታደግ በሚዋደቅበት ወቅት ፈተና ሳይበግራቸውና ከኢትዮጵያዊነት ውኃ ልክ ሳይዛነፉ ማገልገላቸውን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡

በመከላከያ ሚኒስትርነት ሲሠሩ ለነበሩት አብረሃም በላይ (ዶ/ር) ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ አብረሃም በላይ (ዶ/ር) በመከላከያ ሚኒስትርነት ቆይታቸው አመርቂ ስራ መስራታቸውን ተናግረዋል።

ሠራዊታችን ሀገርን ከብተና ለመታደግ በሚዋደቅበት ወቅትም ፈተናዎች ሳይበግሯቸው እና ከኢትዮጵያዊነት ውኃ ልክ ሳይዛነፉ አገልግለዋል ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ለተሾሙት አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል፡፡

የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አብረሃም በላይ (ዶ/ር) በበኩላቸው ለተደረገላቸው የአክብሮት ሽኝት አመሥግነዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.