Fana: At a Speed of Life!

172 ፍልሰተኞችን ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 172 ፍልሰተኞችን ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገለጸ።

በዚህ ሣምንት ኤምባሲውና የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) በትብብር በሦስት ዙር 172 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞችን በአውሮፕላንና በባቡር ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉ ተገልጿል።

የኢትዮ-ጅቡቲ-የመን መንገድ እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ በድንበር ተሻጋሪ ህገ-ወጥ ቡድኖች ምክንያት ዜጎች ለድብደባ፣ እንግልት፣ ዘረፋ እንዲሁም ሞት እየተዳረጉ እንደሚገኙ ኤምባሲው አስገንዝቧል።

ለዚህም ዜጎች ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ከዚህ መሰል አደጋ ለመጠበቅ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት የጋራ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.