Fana: At a Speed of Life!

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ሁለንተናዊ ለውጥ የጎላ ተሳትፎ አላቸው- ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ሁለንተናዊ ለውጥ የጎላ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡

የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚዎችና የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ከክልሉ መንግሥት ጋር በቦንጋ ከተማ እየተወያዩ ነው፡፡

ምክትል ርዕሰ መሥተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ልማትና መልካም አሥተዳደር እንዲሁም በዘላቂ ሠላም ግንባታ ላይ የጎላ አበርክቶ አላቸው፡፡

በቀጣይም መንግሥት በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በትብብር መንፈስ በጋራ የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መንግሥት ችግሮችንና ቁርሾዎችን በውይይት ለመፍታት በጀመረው አካታች ሀገራዊ ምክክር ላይ የነቃ ተሳትፎና ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.