በጄኔራል አበባው ታደሰ የተመራ ልዑክ በጅቡቲ የመከላከያ ሠራዊት 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ታደመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ የተመራ ልዑክ በጅቡቲ የመከላከያ ሠራዊት 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ታደመ፡፡
ክብረ-በዓሉ የጅቡቲ የመከላከያ ሚኒስትር ሀሰን ኦመር መሃመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የመከላከያ ሠራዊት አታሼዎች እና ዲፕሎማቶች በተገኙበት በተለያዩ ወታደራዊ ትርዒቶች ተከብሯል።