Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 ( ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ።

በህንድ በተካሄደው ምርጫ ለሶስተኛ ጊዜ ላሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፤ ምርጫ ህዝብ እውነተኛ የስልጣን ባለቤት መሆኑ የሚገለጥበት ነው ብለዋል።

ወዳጄ ናሬንድራ ሞዲ ሰላማዊ ምርጫ በማካሄድ ለድል በመብቃትዎ እንኳን ደስ ያለዎ በማለት ገልጸው፤ ምርጫው በህንድ የዴሞክራሲ ስርዓት እያበበ መምጣቱን የሚያመላክት መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በደቡብ አፍሪካ ለተካሄደው ነጻ፣ ግልጽና ሰላማዊ ምርጫ ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው የምርጫ ሂደቱ የዴሞክራሲ መርሆዎችን ያከበረ መሆኑን ገልጸው፤ ይህ ደግሞ ለህዝብ ፍላጎትና ለዴሞክራሲ እሴቶች የመገዛት ቁርጠኝነት ነው ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.