ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ የሚያደርጉት ድጋፍ እንዲቀጥል ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጥሪ አቀረበ፡፡
በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ርብርብ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ወደ መጨረሻ ምዕራፍ መሸጋገሩንም ነው የገለጸው ኤምባሲው፡፡
ዳያስፖራው ለግድቡ ግንባታ የፐብሊክ ዲፕሎማሲና አድቮኬሲ፣ የዕውቀትና ክኅሎት ሽግግር እንዲሁም የሀብት ማሰባሰብ ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱንም ኤምባሲው አስታውቋል፡፡
ቀሪ የግንባታ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ግድቡን ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ለማስገባት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስፈልግ በመሆኑ÷ ዳያስፖራው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በለማው https://www.itsmydam.com አማካኝነት የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ኤምባሲው ጥሪ አቅርቧል፡፡