የ6ኛው ዙር ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ ድምጽ መስጫ ቀን ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ6ኛው ዙር ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ ድምጽ መስጫ ጊዜ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ዙር ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ በሚካሄድባቸው÷ የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚገኙ የምርጫ ክልሎች ምርጫ ለማከናወን የተሻሻለ የምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል፡፡