በአዲሱ የስልጣን ዘመኔ ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት አጋርነት ያድጋል – ናሬንድራ ሞዲ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲሱ የስልጣን ዘመኔ ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት አጋርነት እንደሚያድግ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ገለጹ፡፡
በሕንድ በተካሄደው ምርጫ ናሬንድራ ሞዲ ለሦስተኛ ጊዜ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸው ይታወቃል፡፡
ይህን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) ላስተላለፉላቸው መልዕክት አመስግነዋል፡፡
አጋር እንደመሆናችን መጠን ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የሁለትዮሽ ግንኙነት ከፍተኛ ትኩረት ትሰጣለች ብለዋል።
አክለውም ፥ በአዲሱ የስልጣን ዘመኔ ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት አጋርነት ያድጋል ሲሉም ቃል ገብተዋል፡፡