Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ ባሻገር ለልማት ጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ እየተሰጠ ነው – አቶ ሙስጠፌ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የአመራር አንድነትን በማምጣት ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ ባሻገር ለልማት ጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከሀገራዊ ለውጡ በፊት የሶማሌ ክልል ለረጅም ጊዜ በነበረው የሰላም እጦት ሳቢያ ክልሉ በልማት ስራዎች ወደኋላ መቅረቱን አስታውሰዋል።

ሰላም ወዳድ የሆነው የክልሉ ህዝብ ለሰላም ዘብ በመቆም ላለፉት ስድስት ዓመታት በክልሉ በተረጋገጠው ሰላም በሁሉም መስክ ከፍተኛ የልማት እንቅሰቃሴዎች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።

በክልሉ በፊት የነበረው ጎሳን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ሽኩቻ ባህል ተወግዶ፥ ሰላማዊ የፖለቲካ ባህል እና ጠንካራ የአመራር አንድነት መገንባቱንም አስረድተዋል።

ይህም የህዝብን አንድነት በማጠናከር ዘላቂ ሠላም እንዲረጋገጥና የህዝቡን ጥያቄ በተጨባጭ መመለስ ያስቻሉ የልማት ሥራዎች እንዲከናወኑ አስችሏል ነው ያሉት።

በክልሉ ዘላቂ ሰላምንና ልማትን በማረጋገጥ ሂደት ከአመራሩና ከህዝቡ ባሻገር የሀገር ሽማገሌዎችና የጎሳ መሪዎች ተሳትፎ ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም አንስተዋል።

“የሰላም መሰረቱ ልማት ነው” ያሉት ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ÷ የአመራር አንድነትን በመጠበቅ እና ልማትን በማፋጠን ረገድ የክልሉ መንግስት በቀጣይም አበከሮ እንደሚሰራ ለኢዜአ ገልጸዋል።

በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርዎች ጋር ተቀራርቦ የመስራት ባህል እያደገ መምጣቱን ገልፀው÷ ይህን የሰለጠነ የፖለቲካ ሂደት የማጎለበት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

ልዩነቶችን በውይይት መፍታትና የፖለቲካ ፉክክርን በዴሞክራሲያዊ መንገድ በማስቀጠል የክልሉን ሰላም ለማፅናት ሁሉም በቁርጠኝነት እንዲሰራም ጠይቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.