በሐውዜን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰርገኞች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ሐውዜን ወረዳ ሞዚቴ ቀበሌ ትናንት ሰርገኞችን ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲልያፍ በ19 ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሷል፡፡
አደጋው የደረሰው ሙሽራ፣ ሚዜዎች እንዲሁም አጃቢዎችን አሳፍሮ ከአዲሁፃ ወደ ሐውዜን ከተማ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ እና ሞተር ሳይክል በመጋጨታቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚህም የ3 ሰዎች ህይወት ሲልያፍ በ10 ሰዎች ላይ ከባድ በ9 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በዐይደር ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአደጋው ዋና መንስዔም በመጣራ ላይ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡