የተሽከርካሪ የጭስ ብክለት ልቀት መጠን ደረጃ የአፈጻጸም መመሪያ ተዘጋጀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተሽከርካሪ የጭስ ብክለት ልቀት መጠን ደረጃ የአፈጻጸም መመሪያ ማዘጋጀቱን የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
አሽከርካሪዎች የተሽከርካሪውን የጭስ ብክለት ልቀት መጠን በወጣው ደረጃ መሰረት አሟልቶ ማንቀሳቀስ እንዳለባቸው በመመሪያው መመላከቱን የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲዳ ድሪባ አስገንዝበዋል፡፡
የተሽከርካሪ የጭስ ብክለት ልቀት መጠን ሊቀንሱ የሚችሉ አማራጭ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጠቀም እንዳለባቸውም መጠቀሱን ገልጸዋል፡፡
የተሽከርካሪውን የጭስ ብክለት ልቀት መጠን በየዓመቱ የማስመርመር ብሎም ድንገተኛ የጭስ ብክለት ልቀት መጠን ፍተሻ በሚደረግበት ጊዜ ተሽከርካሪውን የማስመርመር ግዴታ እንዳለባቸውም አስረድተዋል፡፡
በአጠቃላይ መመሪያው ከተሽከርካሪ የሚወጣውን የጭስ ብክለት ለመቀነስ የሚያስችል ነው ሲሉ ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡
የበካይ ጋዝ ልቀት መቀነሻ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ተሽከርካሪዎች የሚጠቀሙትን የነዳጅ ፍጆታ ለመቆጠብ እንደሚያስችልም አረጋግጠዋል፡፡