በሜ/ጀ ተስፋዬ አያሌው የተጻፈው “የጀግንነት ሥነ ልቦና” የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሜጀር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው የተጻፈው “የጀግንነት ሥነ ልቦና” የወታደራዊ ሥነ ልቦና ላይ የሚያተኩር መጽሐፍ ተመረቀ፡፡
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሀም በላይ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ከመሰረታዊ ወታደርነት እስከ ከፍተኛ ጀነራል መኮንንነት በታማኝነትና ቅንነት በተለያዩ ኃላፊነቶች እያገለገሉ የሚገኙት ሜ/ጀ ተስፋዬ፤ በማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በሊደርሺፕና መልካም አስተዳደር የሁለተኛ ዲግሪ አላቸው።
በስዊድን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የወታደራዊ ስታፍን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ከፍተኛ የአመራር ኮርሶችን ወስደዋል።
በተመድ የዳርፉር ሰላም ማስከበር ሴክተር ሶስት የዘመቻ ኃላፊ፣ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሀይል የዘመቻና የመረጃ ኃላፊ በመሆንም አገልግለዋል።
ለ30 ዓመታት በዘለቀው ከተዋጊነት እስከ አዋጊነት የወታደራዊ ሀላፊነታቸው ለሀገራቸው ባበረከቱት አስተዋጽኦ ምርጥ የዘመቻ መኮንን ሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በ11 ምዕራፎች በ360 ገፆች የተቀነበበው የጀግንነት ሥነ ልቦና መጽሐፍ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በሶማሊኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀ ሲሆን አቀራረቡም ከታሪካዊ ሥነ ልቦና ዳሰሳ እስከ ንድፈ ሀሳባዊ መርሆዎች የወታደራዊ ሥነ ልቡናን አተገባበር ይተነትናል።
ወታደራዊ፣