Fana: At a Speed of Life!

በደሴ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉአላዊነት እና ክብር’ በሚል መሪ ሀሳብ በደሴ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

ህዝባዊ መድረኩን እየመሩ የሚገኙት የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፤ ጥያቄዎችን በኢትዮያዊነት ማዕቀፍ በሰላምና በሰላማዊ አማራጭ ብቻ እንፈታለን ብለዋል።

ለዚህም ሁሉም የበኩሉን ጥረት ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የመቻቻል ተምሳሌት የሆነችው ደሴ በርካታ የልማት ስራዎችን በማጠናቀቅ ምዕራፍ ላይ እንደምትገኝ ገልጸው፤ ይህንን የተመለከትነውን የልማት ተሞክሮ ሌሎች ከተሞችም ሊወስዱት ይገባል ብለዋል።

በከተማዋ የሚታዩ ልማቶች ሊሰሩ እና ሊጠናቀቁ የቻሉት ማህበረሰቡ በትብብር ከመስራት ባለፈ ለሰላም በሰጠው ትኩረት እንደሆነ አቶ ኦርዲን ተናግረዋል።

ጥያቄዎችን በኢትዮጵያዊ ማዕቀፍ በመፍታት አሁንም ለሰላም ዋጋ በመስጠት ህዝብና መንግስት በጋራ የሚሰሯቸው ልማቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

እሸቱ ወ/ሚካኤል