በአቶ አወሉ አብዲ የተመራ ልዑክ ዲላ ዙሪያ ወረዳ የልማት ስራዎችን ጎበኘ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ የተመራ ልዑካን ቡድን የልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል፡፡
የሥራ ሃላፊዎቹ በጉብኝታቸውም ጎላ ቀበሌ የቡናና የእንሰት ክላስተርን ተመልክተዋል፡፡
ክላስተሩ ወደ ስራ ከገባ በአንድ አመት ጊዜ ወደ የተሻለ ምርት መስጠት የገባ ክላስተር ነው ተብሏል፡፡
ከተረጂነት እና ከጠባቂነት መንፈስ በመላቀቅ በምግብ እራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት በተግባር እያሳዩ የሚገኙ የልማት ስራዎችም መጎብኘታቸው ተገልጿል።
በበረከት ተካልኝ