Fana: At a Speed of Life!

ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በሻሸመኔ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች ከፍተኛ አመራር አባላት በሻሸመኔ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ጎበኙ።

ከፍተኛ አመራር አባላቱ በሻሸመኔ ከተማ በብሻን ጉራቻ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የወተት ከብት ዕርባታና የከብት ማድለብ ማህበራት የስራ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል።

በወተት ከብት እርባታ ላይ የተሰማራ ማህበር ሊቀመንበር አማረ ወርቁ መንግስት ያመቻቸላቸውን የመነሻ ገንዘብና መስሪያ ቦታን በመጠቀም የወተት ላሞችን በማርባት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ቡኔና ረሂማ የከብቶች ማድለቢያ ማህበር አባል ወጣት መሀመድ ቃሲም በበኩሉ÷ ከስንቄ ባንክ ባገኙት አንድ ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ብድር በመታገዝ ልማት ውስጥ ከገቡ አምስት ወር እንዳለፋቸው መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሻሸመኔ ከተማ ግብርና ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማን ማርቆስ÷ በከተማዋ እየተከናወነ ያለው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በመቃኘት የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ጉብኝቱ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

በጉብኝቱም በቢሻን ጉራቻና በመልካ ሶርባ ክፍለ ከተሞች የወተት እና የእንስሳት እርባታ እንዲሁም የእንቁላልና የስጋ ዶሮ እርባታ፣ በከተማ ግብርና ልማት የተከናወኑ ኩታ ገጠም እርሻ ምልከታ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

በጉብኝቱ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል የማህበራዊ ክላስተር ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አብዱልሀኪም ሙለ እና የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዱ ሁሴንን ጨምሮ ሌሎች በየደረጃው ያሉ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.