Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ፊንላንድ የ313 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ፊንላንድ የ5 ሚሊየን ዩሮ (313 ሚሊየን ብር) የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና የፊንላንድ የውጭ ንግድና ልማት ሚኒስትር ቪሌ ታቪዮ ተፈራርመዋል፡፡

ከፈረንጆቹ 2025 እስከ 2028 የሚተገበረው የድጋፍ ስምምነቱ ለመምህራን የቴክኒክ ድጋፍ በማቅረብ አካታች የትምህር ጥራትን እውን ለማድረግ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ የመምህራንን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ተግባራዊ እውቀት እና ክህሎትን ማጎልበት እንደሚያስችልም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.