Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 167 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 167 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

የዛሬ ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ÷ከእነዚህ ውስጥም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 16 ታዳጊዎች እንደሚገኙ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.