Fana: At a Speed of Life!

ሜጀር ጄኔራል ከፍያለው አምዴ ተሰማ በአብዬ ግዛት የተመድ የሰላም አስከባሪ ሃይል አዛዥ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሜጀር ጄኔራል ከፍያለው አምዴ ተሰማን በአብዬ ግዛት የተሰማራው የተመድ የሰላም አስከባሪ ጦር ሀይል አዛዥ አድርገው ሾሙ።

ሜጀር ጄኔራል ከፍያለው አምዴ ተሰማ የስራ ጊዚያቸውን የፊታችን ሀምሌ ወር የሚያጠናቅቁትን ሜጀር ጄኔራል መሀሪ ዘውዴን ተክተው ይሰራሉ ተብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተሰናባቹ ሜጀር ጄኔራል መሀሪ ዘውዴ በትጋት ለሰጡት አገልግሎትና በተመድ ለነበራቸው ውጤታማ የአመራር ጊዜ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተመድ ዋና ፀሃፊ ሹመት የተሰጣቸው ሜጀር ጄነራል ከፍያለው አምዴ ተሰማ በኢትዮጵያ ጦር ውስጥ ከ30 ዓመት በላይ የተለያዩ ወታደራዊ ልምድ እንዳላቸው ተገልጿል።

በቅርብ ዓመታትም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ የኢንጂነሪንግ ክፍልን እንደመሩ እና በአውሮፓውያኑ በ2015 በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ሃይል (አሚሶም) ውስጥ በአመራርነት ማገልገላቸው ተገልጿል።

ሜጀር ጄኔራል ከፍያለው አምዴ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከሩሲያ ጦር አካዳሚ ያገኙ ሲሆን፥ 2ኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በቢዝነስ አድሚኒስተሬሽን ከአሜሪካ አሽላንድ ዩኒቨርሲቲ ማግኘታቸውን ከተመድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.