Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ የጦር ሰራዊቷን ከወታደር  ነጻ ቀጠና ወደ ሆነው ድንበር  እንደምታሰማራ አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰሜን ኮሪያ ጦር ሰራዊቷን ሁለቱን ኮሪያዎች በመክፈል ወደ ተመሰረተው ነጻ የጦር ቀጠና ድንበር ለማስገባት ዝግጅት ማጠናቀቋንና በቅርቡ ተግባራዊ እንደምታደርግ አስጠንቅቃለች።
 
በሳምንቱ መጨረሻ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን እህት ኪም ዮ-ዮንግ ለሠራዊቱ እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ መስጠታቸውን በሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥኝ ቀርበው ተናግረዋል።
 
በዚህም ወታደራዊ ሰራዊቱ ነጻ ወደ ሆነው ዞን ለማስገባት የድርጊት መርሃግብር እየተጠና ነው ብለዋል።
 
ይህን ተከትሎም የሀገሪቱ ጦር ወደ ድንበር ለመጠጋትና ማንኛውንም ውሳኔ በፍጥነትና በጥልቀት ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
 
ይህ እርምጃ በከፊል በደቡብ ኮርያ የሚኖሩና ሰሜን ኮሪያን የከዱ የአርበኞች ግንባር አባላት ለሚልኩት የፕሮፓጋንዳ ቁሳቁሶች በሰሜን በኩል መልኩ ምላሽ ለመስጠት ያለመ መሆኑ ይነገራል።
 
በሁለቱ አገራት መካከል ውጥረቶች እየተባባሱ የመጡት በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ የሰሜን ኮሪያ ዜጎች በፊኛዎች በኩል የሚልኩት ድንበር አቋራጭ ጸብ አጫሪ በራሪ ወረቀቶች እየጨመሩ በመምጣታቸው ነው ተብሏል።
 
የደቡብ ኮሪያ የመከላከያ ሚኒስትር በበኩላቸው÷ የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በቅርብ ለመቆጣጠር ከአሜሪካ ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን በመግለጽ ምላሽ ሰጥቷል ።
 
ይህ ቀጠና ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ በ 1950 ዎቹ የኮሪያ ጦርነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ሁለቱን አገራት የለያየ ነጻ የድንበር ቀጠና ነው ተብሏል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.