1 ሺህ 149 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 149 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።
የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ÷ ከእነሱ ውስጥ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ 10 ታዳጊዎች ይገኙበታል።
ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ42ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።