Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 1445ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በአል በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

በዓሉ ሰላት እና ተክቢራን ጨምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ነው በጅግጅጋ ስታዲየም እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ተወካይና የሶማሌ ክልል ገንዘብ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱረህማን አህመድን ጨምሮ የክልሉ አመራሮች እና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል፡፡

አቶ አብዱረህማን አህመድ÷ ህዝበ መስሊም በዓሉን ሲያከብር በመረዳዳት ፣ በመደጋገፍ እና ይቅር በመባባል መሆን አለበት ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.