Fana: At a Speed of Life!

አቶ እንዳሻው ጣሰው በ2017 ዕቅድ ላይ ከክልሉ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተደድር እንዳሻው ጣሰው በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከመሥተዳድር ምክር ቤት አባላት እና በየደረጃው ካሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሆሳዕና ከተማ እየተወያዩ ነው።

በመድረኩ በጠንካራ የሕዝብ ተሳትፎ አዳዲስ ፕሮጀክቶች መጀመር የሚያስችል፣ ፕሮጀክት የማሥተዳደር አቅም የሚጠናከርበትና የሚያድግበት፣ አደረጃጀቶች አስተማማኝ ደረጃ የሚደርስበትና በላቀ ደረጃ መጠቀም የሚቻልበት እንዲሁም ሁሉም በሥራውና በአፈፃፀሙ የሚለካበት እንዲሆን ታስቦ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ከሕገ-ወጥ አሠራር የጸዳ ተግባር የሚከወንበት፣ በሁሉም ተግባራት የሕብረተሰቡ ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ የሚረጋገጥበት ዕቅድ እንዲሆን መሥተዳድር ምክርቤቱ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ዕቅዱ ስለመታቀዱ መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የተመረጡ የክልሉ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ምክር ቤቱ ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ÷ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ለሥርዓት ግንባታን ትኩረት የሚሰጥ፣ ተቋማትን ማጠናከር ላይ የሚያተኩር፣ ወጥ የሆኑ አሠራሮች የሚተከልበትና የሚጸናበት ሆኖ እንዲዘጋጅ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

እንዲሁም የሕግ ማዕቀፎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ማንዋሎች ሥራ ላይ የሚውሉበት፣ የተጀመሩ የመሰረተ-ልማት ሥራዎችና ፕሮጀክቶች የሚጠናቀቁበት ዕቅድ ሆኖ እንዲዘጋጅ አቅጣጫ መቀመጡ ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.