ኮሮናቫይረስ

ዴክሳሜታሰን መድሃኒት በኮሮና ቫይረስ በፅኑ የታመሙትን ሰዎች ህይወት እንደሚታደግ የብሪታንያ ተመራማሪዎች ገለፁ

By Tibebu Kebede

June 16, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአነስተኛ ዋጋ በስፋት የሚገኘው “ዴክሳሜታሰን” የተባለው መድሃኒት በኮሮና ቫይረስ በፅኑ የታመሙትን ሰዎች ህይወት ለመታደግ እንደሚረዳ የብሪታንያ ተመራማሪዎች ገለፁ።

እንደተመራማሪዎቹ ገለፃ በመድሃኒቱ በአነስተኛ ዶዝ በሚሰጠው የስቴሮይድ ህክምና የኮሮና ቫይረስን በመዋጋት ሂደት ከፍተኛ ውጤት የሚያመጣ ነው።