Fana: At a Speed of Life!

በመቻል 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ላይ የፖርቹጋል ፕሮፌሽናል ስፖርተኞች እንዲገኙ እየሠራሁ ነው – ኤምባሲው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመቻል የስፖርት ቡድን 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ላይ የፖርቹጋል ፕሮፌሽናል ስፖርተኞች እንዲገኙ እየሠራ መሆኑን በኢትዮጵያ የሀገሪቱ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ሊውስ ፍራጎሶ እና የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት የመቻል ስፖርት ቡድንን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም “ቡድኑ በአትሌቲክሰ ስሙ ከፍ ያለ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ነገር ግን ሌሎች የስፖርት አይነቶች እንዳሉት ዛሬ በማየቴ ደስ ብሎኛል” ሲሉ አምባሳደር ሊውስ ፍራጎሶ ገልጸዋል፡፡

የብስክሌት ስፖርት በፖርቹጋል በስፋት እንደሚዘወተር ጠቁመው÷ መቻልም በዘርፉ የሚሠማራ ከሆነ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ እና ፖርቹጋል ግንኙነት በስፖርት፣ ቱሪዝም እና ሥነ-ጥበብ የበለጠ እንዲጠናከር እንሠራለን ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

በመቻል ስፖርት ቡድን 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ላይም የፖርቹጋል ፕሮፌሽናል ስፖርተኞች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አከባበሩን እንዲያደምቁና እንዲታደሙ እየሠራን ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በሚደረገው የጎዳና ላይ ሩጫም እንሳተፋለን ነው ያሉት አምባሳደሯ፡፡

መቻል ስፖርት ቡድን ያለው ታሪክ የሚበረታታ በመሆኑ÷ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በጋራ እንሠራለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር መስፍን በበኩላቸው÷ አንጋፋውና የብዙ ጀግኖች መፍለቂያ ለሆነው መቻል ስፖርት ቡድን 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.