Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው የተባለው የሸገር ታላቁ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው የተባለው የሸገር ታላቁ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በአምስት ዓመታት እንደሚጠናቀቅ የተመላከተው150 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው መንገድ÷ ሁሉንም የሸገር ከተማ ክፍለ ከተሞች እንደሚያገናኝ ተገልጿል፡፡

በመጀመሪያው ዙር በ4 ነጥን 5 ቢሊየን ብር የ38 ነጥብ 5 ኪሎሜትር ግንባታ እንደሚከናወን የተገለጸ ሲሆን÷ ይህም ከኩራ ጅዳ በመነሳት ጣፎ፣ ኮዬ ፈጨ እና ገላን ክፍለ ከተሞችን ያገናኛል ተብሏል፡፡

በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ መንገዶችና ሎጂስቲክ ቢሮ ኃላፊ ሄለን ታምሩ (ኢ/ር)፣ የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው እና ጥሪ የተደረገላቸው ሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.