መድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን አስቻይ ሁኔታ ተዘጋጅቷል- ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መድኃኒት እና የሕክምና ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን አስቻይ ሁኔታዎች መዘጋጀታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ዐውደ-ርዕይን መርቀው ከፍተዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግርም÷ በዐውደ-ርዕዩ የፖሊሲ አውጭዎች፣ አስፈጻሚዎችና አምራቾች የፓናል ውይይቶችን ጨምሮ የልምድ ልውውጦች እንደሚካሄዱ አመላክተዋል፡፡
አሁን ላይ 36 በመቶውን የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓት በሀገር ውስጥ ምርት መሸፈን መቻሉንም አንስተዋል፡፡
”ጤናችን በምርታችን” በሚል መሪ ሐሳብ የተከፈተውን ዐውደ-ርዕይ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ መድኃኒት አምራቾች ማኅበር በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡
ለሥድስት ቀናት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ በሚቆየው ዐውደ-ርዕይ ላይ÷ ከ110 በላይ የዘርፉ አምራቾች እንደሚሳተፉበት ተገልጿል፡፡
በፍሬሕይወት ሰፊው