Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ንግድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በተባበሩት የታንዛንያ ሪፐብሊክ በዛንዚባር እየተካሄደ በሚገኘው 14ኛው የአፍሪካ ንግድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

በስብሰባው ላይ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)እየታደሙ ነው፡፡

ስብስባው በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት አተገባበር ያስገኛቸው ጠቀሜታዎችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ ምክክር በማድረግ ትግበራው በሚፋጠንበት አግባብ ላይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚኒስትር ዴኤታው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልፀዋል፡፡

ካሳሁን(ዶ/ር) ኢትዮጵያ የእቃዎች አቅርቦት ዝርዝር አቅርባ በ13ኛው የአፍሪካ ንግድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ማፀደቋን አስታውሰዋል፡፡

አሁን ላይ የሙከራ ንግድ ለመጀመር የሚያስችል የሁለትዮሽ ውይይቶች ከተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ጋር የሚደረግ መሆኑንም ነው የጠቆሙት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.