Fana: At a Speed of Life!

በባሕር ዳር ከተማ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ባሕር ዳር ከተማ ”ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡

በኮንፈረንሱ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና የአማራ ክልል ም/ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬን ጨምሮ የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

እንዲሁም የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ እና ሌሎች የጦር መኮንኖችም በኮንፈረንሱ ተሳትፈዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሲቪክ ተቋማት መሪዎች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ተወካዮች የተገኙበት መድረኩ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ አሚኮ ዘግቧል፡፡

በኮንፈረንሱ በክልሉ በተከሰተው የሰላም እጦት እና የመፍትሔ ሀሳቦች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.