አምባሳደር ታዬ ከኢጋድ ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
ዋና ጸሃፊው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ከአምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ጋር ጅቡቲ በሚገኘው የኢጋድ ዋና መሥሪያ ቤት ተገናኝተን ተወያይተናል ብለዋል፡፡
በዚህም በጋራ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ጠቁመው÷በተለይም በወቅታዊው የሱዳን ጦርነት ዙሪያ መወ ያየታቸውን አንስተዋል፡፡
አምባሳደር ታዬ ኢጋድ በቀጣናው ተልዕኮውን ለመወጣት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውንም ጠቅሰዋል፡፡