ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ችግኝ ስንተክል ለኢኮኖሚ ዘርፎችም ጉልበት እየጨመርን ነው አሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ችግኝ ስንተክል ለሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ጉልበት እየጨመርን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡
ዛሬ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ ማስጀመራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም “እኛ ስንተክል ሀገርን አረንጓዴ እያለበስን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ጉልበት እየጨመርን ነው” ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብሩን ከማስጀመራቸው ቀደም ብሎ በደሴ ከተማ እና አካባቢው እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን መጎብኘታቸው እና ከደሴ ከተማ ከተውጣጡ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር መወያየታቸው ይታወቃል፡፡