ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የለጎ ሐይቅ ፕሮጀክትን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በትጋት እየተሠራ መሆኑን አረጋገጡ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በገበታ ለትውልድ እየለማ የሚገኘውን የለጎ ሐይቅ ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ግንባታው ሲጠናቀቅ ወሎና አካባቢውን የቱሪስት መዳረሻ እንደሚያደርገውም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የገለጹት፡፡
ፕሮጀክቱ ከወዲሁ ለበርካቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን አስረድተው÷ ግንባታውን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በትጋት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል፡፡