Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 169 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 169 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ለተመላሽ ወገኖችም ድጋፍ እየተደረገና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ ከ52 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያን ተመልሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.