Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በዶንባስ ክልል የሚገኝ ተጨማሪ ግዛት መቆጣጠሯን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በዶንባስ ክልል የሚገኝ ተጨማሪ ግዛት መቆጣጠሯን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ኖቮፖክሮቭስኮይ በመባል የሚጠራው የዶኔስክ መንደር ከዩክሬን ሃይሎች ሙሉ በሙሉ ነጻ መደረጉን አረጋግጧል፡፡

የሩሲያ ማዕከላዊ ሃይሎች በመባል የሚጠራው ወታደራዊ ክፍል በአካባቢው በወሰደው ፈጣን እርምጃ ነው የዩክሬን ወታደሮች ከአካባቢው እንዲጸዱ የተደረገው፡፡

እርምጃው የሩሲያ ወታደራዊ ሃይል በአካባቢው አቋሙን እንዲያሻሽል እና ወታደራዊ ስልቱን እንዲያጠናክር ያስችለዋል ተብሏል፡፡

በዶኔስክ ክልል ቻሶቭ ያር፣ ቶሬስክ እና ኡሮዝሃይኖዬ በተሰኙ አካባቢዎች የሚደረገው ውጊያ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

በሩሲያ እንደሚደገፉ የሚነገርላቸው የዶንባስ ክልል ታጣቂዎች በ1 ሺህ 45 የዩክሬን ወታደሮች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውንም አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.