Fana: At a Speed of Life!

የሆቴሎች የኮኮብ ደረጃ ምደባ በአዲስ መልክ ሊሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሆቴሎች የኮኮብ ደረጃ ምደባ በአዲስ መልክ ሊሰራ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከመስከረም ጀምሮ ከዚህ በፊት የተሰጠው የኮከብ ደረጃ ሥራ ላይ እንደማይውልም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡

በሚኒስትሮች ም/ቤት የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የደረጃ ምደባ ደንብ ቁጥር 173/2002 መሰረት ደረጃ የተሰጣቸው ሆቴሎች በየሶስት ዓመት ዳግም በደረጃ መመደብ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡

በዚህ መሰረትም ሚኒስቴሩ በአዲስ አበባ ከተማ እና በክልሎች ለሚገኙ ሆቴሎች ዳግም የደረጃ ምዘና ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለው መመሪያ ላይ ከሆቴል ባለቤቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማካሄዱንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚሁ ወቅት የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ÷አሁን በሚያደረገው የዳግም ደረጃ ምዘና ሒደት ውስጥ የማያልፉ ሆቴሎች ከዚህ ቀደም የተሰጣቸው የኮከብ ደረጃ በህጉ መሰረት የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ በመሆኑ የኮከብ ደረጃው እንደሚሰረዝ ተናግረዋል፡፡

ዳግም ምደባው በዋናነት ሆቴሎች የሚሰጡትን አገልግሎት ማሻሻል እና የሀገሪቱን የቱሪዝም አገልግሎት ተወዳዳሪነት ማሳደግ ላይ እንደሚያተኩርም ገልፀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.