በአቶ አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ ሐረር ገባ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የፌዴራል አመራሮች ልዑክ ሐረር ከተማ ገብቷል፡፡
ልዑኩ ሐረር ከተማ ሲደርስ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ እና የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ሱልጣን አብዱሰላምን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች አቀባበል አድርገውለታል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላትም ከነገ ጀምሮ በሚከበረው 26ኛው ዓለም አቀፍ የሐረር ቀን ላይ እንደሚታደሙ መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡