Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ያለባት የውጭ እዳ ወደ 17 ነጥብ 5 በመቶ ዝቅ ብሏል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ያለባት የውጭ እዳ ወደ 17 ነጥብ 5 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው በ2016 በጀት ዓመት በእያንዳንዱ ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል፡

የኢትዮጵያ ያለባት የውጭ እዳ ወደ 17 ነጥብ 5 በመቶ ዝቅ ማለቱንም ነው የገለጹት፡፡

በቀጣይ ዓመታት በሚደጉ ርብርቦች ከ10 በመቶ በታች ማውረድ እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ላለፉት ስድስት ዓመታት ምንም አይነት ኮሜርሺያል ብድር እንዳልተወሰደም አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.