Fana: At a Speed of Life!

“ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም!” ሀገር አቀፍ የጎዳና ሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰላምን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሀገር አቀፍ የ6 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ነው።

ውድድሩ “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም!” በሚል መሪ ሀሳብ ከማለዳ 12 ሠዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና በሌሎች ዋና ዋና የክልል ከተሞች በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ የሰላም ሩጫ መርሐ ግብር በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎች እየተሳተፉ መሆኑ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው መርሐ ግብር ታዋቂ አትሌቶችና ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች እየተሳተፉ መሆኑ ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.