Fana: At a Speed of Life!

ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እንሮጣለን – አቶ እንዳሻው ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የማያቋርጥ ሩጫ እንሮጣለን ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም በሚል መሪ ሐሳብ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሂዷል፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ የጎዳና ላይ ሩጫውን ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የማያቋርጥ ሩጫ እንሮጣለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በሀገሪቱ የተጀመረው ዘላቂ ሰላም እውን እንዲሆን የሁሉንም ኢትዮጵያዊ የጋራ ጥረት እንደሚጠይቅም አስገንዝበዋል፡፡

ሰላምን ማጠናከር እና ለሰላም ዘብ መቆም ይገባል ማለታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽንቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ምንም እንኳን ያሳለፍናቸው አስቸጋሪ ጊዜያት ቢኖሩም ያለፈውን ረስተን ወደ ፊት ስላለው ብሩህ ጊዜ ማሰብ ይገባል ብለዋል፡፡

በትብብር እና በጋራ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ ሁሉም መትጋት እና መረባረብ እንደሚጠበቅበትም ነው ያስረዱት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.