በ500 ሚሊየን ብር ለሚገነባው ሆስፒታል የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ጎርቼ ወረዳ በ500 ሚሊየን ብር ለሚገነባው የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የመሠረት ድንጋይ አኖሩ።
የሆስፒታሉ ግንባታ ሲጠናቀቅም 100 ሺህ ለሚሆኑ የጎርቼ ወረዳና አካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ባለሁለት ወለል የሆነውን የሆስፒታሉን ሕንጻ ግንባታ፣ የሕክምና ማሽነሪና ቁሳቁስ ግዢውንና ሌሎች ወጪዎቹን አጠቃሎ 500 ሚሊየን ብር ወጪ ይጠይቃል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡