የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን በወላይታ ሶዶ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ÷ መድረኩ ለስራ ምቹ የሆነ ክልል ከመፈጠር አኳያ በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገም እና ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እንዲሁም መታረም ያለባቸውን ጉድለቶቸን ለይቶ ማረም የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
መስተዳድር ምክር ቤቱ በዛሬው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው በዋነኛነት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን የሚገመግምና የ2017 ዕቅድ ዝግጅት ዙሪያ በመነጋገር ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ምክር ቤቱ በተጨማሪ የ2017 በጀት ዓመት የበጀት ድልድል መነሻ ሃሳቦች ላይ እንዲሁም የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችና ደንቦች ላይ በመወያየት ውሳኔ የሚያሳልፍ ይሆናል።
በምክር ቤቱ ስብሰባ የክልሉ መንግስት የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀመ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝ ከክልሉ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡