የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከ20 ቢሊየን ዶላር በላይ የወጪ ንግድ ምርት የማመንጨት አቅም እንዳለው ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከ20 ቢሊየን ዶላር በላይ የወጪ ንግድ ምርት የማመንጨት አቅም እንዳለው ተጠቁሟል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የተጠሪ ተቋማትን የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸምን ገምግመዋል።
በወቅቱም÷ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከ20 ቢሊየን ዶላር በላይ የወጪ ንግድ ምርት የማመንጨት አቅም እንዳለው ተናግረው፤ ይህን እድል ለመጠቀም አሰራሮችን ዘመናዊ ማድረግ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አሰራሮችን በማዘመን ህገ ወጥነትን ማስቀረት ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህም ሀገሪቱ በኢኮኖሚው ዘርፍ ማግኝት ያለባትን ገቢ እንድታገኝ አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።