Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ17 ቀናት ቆይታ በኋላ ኤሌክትሪክ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ላለፉት 17 ቀናት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ተቋርጦ የቆየው ኤሌክትሪክ ዳግም መገናኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡

በተቋሙ የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች የኦፕሬሽን ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሃብታሙ ውቤ እንደገለፁት÷ ተቋርጦ የቆየው የኤሌክትሪክ ሃይል እንዲመለስ ለማድረግ እልህ አስጨራሽ ጥረቶች ተደርገዋል።

ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገቡ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ ተደጋጋሚ ስርቆት ስለሚፈፀም የተቋረጠውን ኃይል መልሶ የማገናኘት ሥራውን ፈታኝ አድርጎት ቆይቷል ብለዋል።

ለቀናት መስመሩን ለማገናኘት የተደረገው ጥረት ተሳክቶ ዛሬ ከቀኑ 9፡05 ሰዓት ጀምሮ አካባቢዎቹ ኤሌክትሪክ ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

በጥገና ሥራው ላይ ድጋፍ ላደረጉት የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ለሁለቱ ክልሎች መስተዳድሮች እና ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ምስጋና ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.